
የአካል ብቃት እቅስቃሴ ማድረግ ለጤናማ ሕይወት መሰረትና ለጥሩ እና ሰላማዊ እንቅልፍዎ ተመራጭ መፍትሔ ነው፡፡ ነገር ግን እንቅልፍ ከመተኛትዎ በፊት በ3 ሰዓታት ውስጥ የሚሰሩ ከሆነ የሰውነት ሙቀት መጠንዎ ስለሚጨምር እና በቶሎ ለመቀዝቀዝ ጊዜን ስለሚፈጅ ለመተኛት ይቸገራሉ፡፡ ስለዚህም አካል ብቃት እንቅስቃሴ በጠዋት ቢሰሩ ይመከራል፡፡

ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ከነዚህ ቁሳቁሶች የሚመጣ ከፍተኛ ብርሃን ሰውነታችን እንቅልፍ እንድንተኛ የሚረዳን ሆርሞን (ሜላቶኒን) እንዳይመነጭ ስለሚያደርግ እንቅልፍ ከመተኛትዎ ከአንድ ሰዓት በፊት ቴሌቪዢንዎን/ኮምፒተርዎን/ማጥፋት አይዘንጉ፡፡

እንደ አካል ብቃት እንቅስቃሴ ሁሉ የሙቅ ሻወር መውሰድ ጥሩ እንቅልፍ እንዲተኙ የሚረዳ ሲሆን ለእንቅልፍ ችግር የሚሆነው ግን ከመተኛትዎ እጅግ ቀርቦ ሲተገብሩት ነው፡፡ የሰውነት ሙቀት እጅግ ከጨመረ ለመተኛት ሰለሚቸገሩ ሰውነትዎ እስኪቀዘቅዝ ጊዜ ይስጡ፡፡

ካፌን ያላቸውና አልኮል መጠጦችን መውሰድ ሰላማዊ ቅንቅልፍ እንዳይወስድን የሚዳርጉ ሲሆን፣ ከዚህ በተጨማሪ ማንኛውንም ዓይነት ፈሳሽ ከአንድ ወይንም ሁለት ሰዓታት በፊት መውሰድ የውሃ ሽንት ለማስወገድ ከአንዴ በላይ እንዲነሱ ስለሚያደርግ አይመከርም፡፡ይህ ሲባል ግን እየጠማዎት ይተኙ ማለትም አይደለም፡፡ ምክንያቱም ውሃን ለመጠጣት መነሳትዎ አይቀርምና ስለዚህ ቀደም ብለው ተጥተው እና የውሃ ሽንት አስወግደው ሰላማዊ እንቅልፍ መተኛት ይችላሉ፡፡

በተቻለ መጠን ሥራዎን በጊዜ ለማጠናቀቅ ይሞክሩ ምክንያቱም ሥራን ዘግይቶ/አምሽቶ መስራት አንጎልዎን የማነቃቃትና ላልተፈለገ ጭንቀትም ሊዳርግዎ ስለሚችል ነው፡፡

አብዛኛውን ጊዜ አጓጊ እና ልብ አንጠልጣይ ልብ ወለዶችን ማንበብ እንቅልፍ ከመተኛት ሊያግዱን ይችላሉ ወይንም ከለመድነው ሰዓት እጅግ እንድንዘገይ ያደርጋሉ ይህም ሰውነታችን የሚገባውን የዕረፍት መጠን ስለሚሻ እንቅልፍ ሳንጨርስ መነሳት ለተቀረው ቀን የሚኖረንን ውጤታማነት በእጅጉ ይቀንሳል፡፡

ከጥጋብ በላይ መመገብ እንዲጨነቁና እንቅልፍ በቶሎ እንዳይወስድዎ ስለሚያደርግ እራት ሲመገቡ በልኩ ቢሆን ይመከራል፡፡ጨው የበዛባቸው ምግቦችን በአራት ሰዓት መመገብ ሌሊት በውሃ ጥማት ስለሚቀሰቅስዎ እንዲመገቡ አይመከርም፡፡

እንቅልፍ ለመተኛት ቢያስቡ አዕምሮዎን ነጻ አድርገው መሆን ይኖርብዎታል፡፡ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከጥል ወይንም ከአስደንጋጭ አጋጣሚ በኋላ ወዲያውኑ ለመተኛት እጅግ እንደምንቸገር ነው፡፡ ስለዚህ የሚፈታ ችግርም ካለ በጊዜ ተነጋግሮ ችግሩን መፍታት ለሰላማዊ እንቅልፍ ወሳኝ ነው፡፡
—————————-
ምንጭ – ዶ/ር ሆነልያት
ምንጭ – ዶ/ር ሆነልያት
No comments:
Post a Comment