Pages

Tuesday, 5 September 2017

በስራ መሰላቸት




By Besufkad Zena
በስራ መሰላቸት በስራቸው ታታሪ የሆኑ ሰዎችን የሚያጠቃ በስራቸው ደስተኛ እንዳይሆኑ የሚያደርግ ነው፡፡ስለትልቅ ሰው ሰይኮሎጂ ሲወራ ትኩረት ከሚሰጣቸው ነገሮች መሀከል አንዱ በስራ መሰላቸት ነው፡፤አንድ ሰው በስራ ተሰላቸ የሚባለው ሀይለ ስሜታዊ፣ አእመሮአዊ እና አካላዊ ዝለት
ሲሰማው ነው፡፡በዚህም የተነሳ ሰዎች ስራቸውን በአግባቡ ያለመቻል ስሜት፣ፍላጎት እና ተነሳሽነት ማጣት ሊታይባቸው ይችላል፡፡በስራ መሰላቸት (መቃጠል) ውጤታማነትን እና ጉልበትን ይቀንሳል፡፡ እንዲሁም የተስፋ ቢስነት እና አቅም የማጣት ስሜት እንዲሰማን ያደርጋል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሰዎች በሚሰሩት ስራ በጣም በመሠላቸታው የተነሳ ሙሉ ለሙሉ ወደሌላ ስራ ሊገቡ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ ከአስተማሪነት ወደ ግንበኝነት ወይም ዶክተር የሆነ ሰው ወደ ንግድ ሊሄድ ይችላል፡፡ ...በስራ መሰላቸት(መቃጠል) በማህበራዊ ህይወታችን እና ከቤተሰባችን ጋር ያለን ግንኙነት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ያሳድራል እነዲሁም በቀላሉ በጉንፋን እና በመሰል በሽታዎች ልንጠቃ እንችላለን፡፡
በስራ መሰላቸትን የሚያስከትሉ ምክንያቶች
በስራ መሰላቸትን ሊያስከትል የሚችሉ ብዙ ምክንቶች አሉ የተለያዩ የጥናት ውጤቶች እነደሚሳዩት እንዚህን ምክንያቶች ከስራ ጋር ግንኙነት ያላቸው፣ከአኗኗር ዘዴያችን ጋር ግንኙነት ያላቸው እና ከስብእናችና ጋር ግኝኙነት ያላቸው ተብለው በ3 ይከፈላሉ፡፡
1.ከስራ ጋር ግኝኙነት ያላቸው ምክንያቶች
• ስራችን ላይ ሌላ ሰው ጣልቃ እየገባ እንደሆነ ከተሰማን
• ለሰራነው ጥሩ ስራ እውቅንና እና ሽልማት ሲነፈገን
• ግልጽ ያልሆነና እና ከመጠን ያለፈ የሥራ ጫና ሲኖርብን
• የምንሰራው ስራ ሁሌ አንድ አይነት ሲሆንብን እና አዲስ ነገር ሥናጣበት
• እውነታን ያላገናዘበ እና ከአቅም በላይ የሆነ ውጤት እንድናመጣ የሚጠበቅብን ከሆነ

2. ከአኗኗር ዘይቤያችን ጋር ግንኙነት ያላቸው ምክንያቶች
• ለማህበራዊ ህይወት እና ለመዝናናት የሚሆን ሰአት ከሌለን እና ዝም ብለን ስራ ላይ የምንጠመድ ከሆነ፡፡
• ብዙ ነገሮችን በአንድ ጊዜ ለማሳካት የምንሞክር ከሆነ
• ብዙ ሃላፊነቶችን የሚያግዘን ሰው ሳይኖር በአንዴ የምንቀበል ከሆነ
• በቂ እንቅልፍ የማናገኝ ከሆነ
3.ከስብእናችን ጋር ተያያዥነት ያላቸው ምክንያቶች
• ከምንሰራው ስራ ፍጽምነትን መጠበቅ
• ስለ ስራ እና ስለህይወት አሉታዊ እይታ መኖር
• ስራችንን ለመስራት የሌላ ሰዎችን ግፊት እና ቁጥጥር መጠበቅ
• ትልቅ ስኬትን የማሳካት ጉጉት
በስራ የተሰላቹ ሰውች የሚያሳያአቸው ምልክቶች
በስራ መሰልቸት(መቃጠል) በአንድ ጊዜ የሚከሰት ነገር ሳይሆን በጊዜ ሂደት እየጨመረ የሚመጣና በምንሰራው ስራ በምንኖረው ኑሮ ከሰዎች ጋር ባለን ግኝኙነት ደስተኛ እንዳንሆን የሚያደርግ ነገር ነው፡፡ ብዙ ምልክቶች ያሉት ሲሆን እነዚህን ምልክቶች አካላዊ፣ሐይለስሜታዊ እንዲሁም ባህሪያዊ ብለን በሶስት እንከፍላቸዋለን
1.አካላዊ ምልክቶች
• በአብዛኛው ጊዜ የድካም ስሜት የሚሰማን ከሆነ
• የበሽታ መከላከል ሀይላችን መዳከም እና የህመም ስሜት
• ተደጋጋሚ የሆነ እራስ ምታት፣የጡንቻ እና የወገብ ህመም የመሰማት ስሜት
• የምግብ ፍላጎት እና የእንቅልፍ ልማድ መቀየር
2.ሐይለስሜታዊ ምልክቶች
• የውድቀት ስሜትና እራስን መጠራጠር
• የሽንፈት እና አቅም የማጣት ስሜት
• የብቸኝነት ስሜት
• ተነሳሽነት ማጣት
• ከመጠን ያለፈ አሉታዊ አመለካከት
• በምንሰራው ስራ እርካታ ማጣት
3.ባህሪያዊ ምክንያቶች
• ሀላፊነትን መሸሽ
• ገለልተኛ መሆን
• አልኮል፣ሲጋራ እና ጫት የመሳሰሉ ነገሮችን መጠቀም
• ተገልጋይ ላይ መበሳጨት እና መመነጫጨቅ
• አርፍዶ ስራ መግባት
በስራ መሰልቸትን(መቃጠልን) እንዴት መከላከል ይቻላል
• ስራን ለመስራት ከመጀመራችን በፊት እራሳችንን የምናዝናናበት ነገር ይኑረን
• የተስተካከለ የአመጋገብ፣የአተኛኘት እንዲሁም እስፖርት የመስራት ልማድ ይኑረን
• እራሳችንን ከሚገባው በላይ አንበታትን መስራት የምንነረችለውን ነገር እንወስን
• ኮምፒውተር እና መሰል ከሆኑ መሳሪያዎች ጋር ያለንን መስተጋብር እንቀንስ
• ጭንቀትን መቋቋያ ዘዴዎች እንለማመድ
• የምንችል ከሆነ ስራችችንን መስሪያ ቤት ጨርሰን እንውጣ እቤታችን ስንገባ ከስራ ውጪ የሆነ ነገር ላይ እንጠመድ
• የአመት እረፍታችንን በአግባቡ እንጠቀም የአመት እረፍት በስራ መሰላቸትን(መቃጠልን) ለመቀነስ የሚረዳ ትልቅ መሳሪያ ነው፡፡አንዳንድ ሰዎች የአመት እረፍታቸውን በገንዘብ እንዲለወጥላቸው ሲያደርጉ ይስተዋላሉ እንደዚህ ማደረጉ ለመስረያ ቤቱም ይሁን ለሰራተኞቹ ብዙ አይጠቅምም፡፡ ከዚህ ይልቅ ሰዎች በግድ እረፍት እንዲወጡ ቢደረጉ እና አእምሮአቸውን አድሰው በአዲስ መንፈስ ቢመለሱ በስራ መቃጠልን ከመከላከላቸው በተጨማሪ ውጤታማ የመሆን እድል አላቸው፡፡

No comments:

Post a Comment